መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘዳግም 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በምድር በዳ በዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ሜዳ በዓረባ፥ በፋራን፥ በጦፌል፥ በላባን፥ በሐጼሮት፥ በዲዛሃብ መካከል ሳሉ፥ ለአስራኤል ሁሉ የተናገራቸው እነዚህ ቃላት ናቸው።
2በሴይር ተራራ መንገድ ከኮሬብ እስከ ቃዴስ በርኔ ድረስ የአሥራ አንድ ቀን ጉዞ ነው።
3በአርባኛው ዓመት በአሥራ አንደኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሙሴ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ያዘዘውውን ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ ነገራቸው።
4ይህም እግዚአብሔር በሐሴቦን ይኖር የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ በአስታዎትና በኤድራይ ይኖር የነበረውንም የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከመታ በኋላ ነበር።
5በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ምድር ሙሴ እንዲህ ብሎ እነዚህን መመሪያዎች ይናገር ጀመር፦
6እግዚአብሔር አምላካችን በኮሬብ እንዲህ ብሎ ተናገረን፦ በዚህ ተራራ የኖራችሁበት ይብቃችሁ።
7ጉዞኣችሁን ወደ ኮረብታማው ወደ አሞራውያን አገር ወደ ድንበሮቹም፥ ሁሉ በዓረባም በደጋውና በቆላው፥ በደቡብና በባሕር ዳር ወዳሉ ወደ ከነዓናውያን ምድር፥ ወደ ሊባኖስ ወንዝ ሸለቆ እስከ ታላቁ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ሄዱ።
8እነሆ ምድሪቱን በፊታችሁ አድርጌአለሁ፤ እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ፥ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣቸው ዘንድ የማለላቸውን ምድር ሂዱና ውረሱ።
9በዚያን ጊዜ እንዲህ ብዬ ተናግሬአችሁ ነበር፦ እኔ በራሴ ብቻዬን ልሸከማችሁ አልችልም።
10እግዚአብሔር አምላካችሁ አብዝቶአችኋል፥ እነሆም እናንተ ዛሬ እንደ ሰማይ ከዋክብት ብዙ ናችሁ።
11የአባቶቻችሁ እግዚአብሔር አምላክ ሺህ ጊዜ ሺህ ያድርጋችሁ፤ ተስፋ እንደሰጣችሁም ይባርካችሁ።
12ነገር ግን እኔ በራሴ ድካማችሁን፥ ሸክማችሁንና ክርክራችሁን እሸከም ዘንድ ብቻዬን እንዴት እችላለሁ?
13ከእናንተ መካከል ከየነገዶቻችሁ ጥበበኞች፥ አስተዋዮችና አዋቂዎች የሆኑትን ሰዎች ምረጡ፤ እኔም እነርሱን የእናንተ አለቆች አደርጋቸዋለሁ ብዬኣችሁ ነበረ።
14እናንተም እንዲህ ብላችሁ መለሳችሁ፦ የተናገርከንን ነገር ለማድረግ ለእኛ መልካም ነው።
15ስለዚህም ጥበበኞችና አዋቂዎች የሆኑትን የነገዶቻችሁን ወሰድሁ፥ በእናንተም ላይ አለቆች እንዲሆኑ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የአምሳ አለቆች፥ የአሥር አለቆችና ሹማምንት በየገዶቻችሁ አደረግኋቸው።
16በዚያን ጊዜም ፈራጆቻችሁን እንዲህ ብዬ አዘዝኳቸው፦ በወንድሞቻችሁ መካከል፤ በሰውና በወንድሙ መካከልና በመጻተኛ ላይ በጽድቅ ፍረዱ።
17በክርክርም ጊዜ ለማንም ፊት አድልዎ አታድርጉ፥ ታላቁን እንደምትሰሙ፥ ታናሹንም ስሙ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለሆነ የሰው ፊት መፍራት አይገባችሁም። ከክርክርም አንድ ስንኳ ቢከብዳችሁ ወደ እኔ አምጡት እኔም እሰማዋለሁ።
18በዚያን ጊዜም ልታደርጉት የሚገባችሁን ነገር ሁሉ አዘዝኋችሁ።
19ከኮሬብም ተነስተን፥እግዚአብሔር አምላካችን እንዳዘዘን እንዳያችሁትም በታላቁና እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ምድረ በዳ ሁሉ ተጉዘን በተራራማው በአሞራውን አገር ሄድን፥ ወደ ቃዴስ በርኔም መጣን።
20እኔም እንዲህ አልኋችሁ፦ እግዚአብሔር አምላካችን ወደ ሚሰጠን ወደ ተራራማው አሞራውያን አገር መጣችኋል።
21እነሆ እግዚአብሔር አምላካችሁ ምድሪቱን በፊታችሁ አድርጎአል፤ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር እንዳላችሁ ውጡ፥ ውረሱአት፥ አትፍሩ አትደንግጡም።
22ከእናንተም ሁላችሁ ወደ እኔ መጥታችሁ እንዲህ አላችሁ፦ ምድሪቱን እንዲሰልሉልንና እናጠቃቸው ዘንድ የሚገባንን የመንገዱንና የምንገባባቸውን ከተሞች ሁኔታ ተመልሰው እንዲነግሩን ከፊታችን ሰዎችን እንድስደድ።
23ነገሩም ደስ አሰኘኝ፤ ከእናንተም ከየነገዱ ሁሉ አንድ አንድ ሰው፥ አሥራ ሁለት ሰዎችን መረጥሁ።
24እነርሱም ወደ ተራራማው አገር ሄዱ፥ ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጥተው ሰለሉአት።
25እነርሱም ከምድሪቱ ፍሬ በእጃቸው ወሰዱ፥ ወደ እኛም ይዘውት መጡ። እነርሱም ደግሞ፦ እግዚአብሔር አምላካችን የሚሰጠን ምድር መልካም ናት ብለውም አወሩልን።
26ምድሪቷንም ማጥቃት እንቢ ብላችሁ፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐመፃችሁ፥ ።
27በድንኳናችሁም ውስጥ እንዲህ እያላችሁ አጉረመረማችሁ፦ እግዚአብሔር ስለ ጠላን እንዲያጠፋን በአሞራውያን እጅ አሳልፎ ይሰጠን ዘንድ ከግብፅ ምድር አወጣን።
28አሁን ወዴት መሄድ እንችላለን? ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ቁመቱም ከእኛ ይረዝማል ከተሞቹም ታላላቆች፥ የተመሽጉና እስከ ሰማይም የደረሱ ናችው፥ የዔናቅንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው፤ ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን እንዲቀልጥ አደረጉ።
29እኔም አልኋችሁ፦ አትደንግጡ፥ እነርሱንም አትፍሩአቸው።
30በፊታችሁ የሚሄደው እግዚአብሔር አምላካችሁ ስለ እናንተ ይዋጋል፥ በፊታችሁም በግብፅና በምድረ በዳ እንዳደረገላችሁ ሁሉ፤
31ወደዚህም ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በሄድዳችሁበት መንገድ ሁሉ ሰው ልጁን እንደሚሸከም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተሸከማችሁ እናንተ አይታችኋል።
32ዳሩ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁን በዚህ ነገር አላመናችሁትም፤
33በፊታችሁም ሆኖ በምትሄዱበት መንገድ ድንኳናችሁን እንድታቆሙ ቦታ እንድታገኙና በሌሊት በእሳት፥ በቀንም በደመና እንድትሄዱ መንገዱን ያሳታችሁ እርሱ ነው።
34እግዚአብሔርም የቃላችሁን ድምፅ ሰምቶ ተቆጣ፥ ምሎም፥ እንዲህ አለ፦
35በርግጥ ለአባቶቻችሁ እሰጣቸው ዘንድ የማልሁላቸውን መልካሚቱን ምድር ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በቀር ከእነዚህ ሰዎች ከዚህ ክፉ ትውልድ ማንም አያይም።
36እርሱም እግዚአብህሔርን ፈጽሞ ተከትሎአልና የረገጣትን ምድር ለእርሱና ለልጆቹ እሰጣለሁ ብሎ ማለ።
37እግዚአብሔርም ደግሞ በእናንተ ምክንያት እኔን ተቆጣኝ እንዲህም አለ፦ አንተ ደግሞ ወደዚያ አትገባም
38በፊትህ የሚሄድ አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ወደዚያ ይገባል፥ እርሱም እስራኤላውያን ምድሪቱን እንዲወርሱ ይመራቸዋልና፤ አደፋፍረው።
39ከዚህም በተጨማሪ፦ ለጉዳት ይዳረጋሉ፥ ዛሬም መልካሙንና ክፉውን መለየት የማይችሉ ናቸው ያላችኋችሁ ታናናሽ ሕፃናታችሁ ልጆቻችሁ እነርሱ ወደዚያ ይገባሉ። ምድሪቱንም ለእነርሱ እሰጣለሁ ይወርሱታልም።
40እናንተ ግን ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።
41እናንተም፦ እግዚአብሔርን በድለናል፥ እግዚአብሔር አምላክችሁ እንዳዘዘን ሁሉ እንወጣለን፥ እንዋጋማለን ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ከእናንተም ሰው ሁሉ የጦር መሣሪያውን ያዘ፥ ወደ ተራራማውም አገር ለመውጣትና ለማጥቃት ተዘጋጀ።
42እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ እኔ በእናንተ መካከል ስለማልገኝ፥ በጠላቶቻችሁ ፊት እንዳትሸነፉ አትውጡ፥ አትዋጉም በላቸው አለኝ።
43እኔም ተናገርኋችሁ እናንተም አልሰማችሁም። በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐመፃችሁ፥ አልሰማችሁም በትዕቢታችሁም ወደ ተራራማው አገር ለማጥቃት ወጣችሁ።
44ነገር ግን በተራራማው አገር ይኖሩ የነበሩ አሞራውያን በእናንተ ላይ ወጥተው እንደ ንብ አሳደዱአችሁ፥ እስከ ሔርማም ድረስ በሴይር መቱአችሁ።
45ተመልሳችሁም በእግዚአብሔር ፊት አለቀሳችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ድምፃችሁን አልሰማም፥ ወደ እናንተም አላዳመጠም።
46ሁሉም ቀናት በቆያችሁባችሁ ለብዙ ቀን በቃዴስ ተቀመጣችሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።