1ሽማግሌው በእውነት ለምወደውና ለተወደደው ጋይዮስ።
2የተወደድክ ሆይ በነፍስህ እንደበለጸግህ በሁሉ ነገር እንድትበለጽግና በመልካም ጤንነት እንድትሆን እጸልያለሁ።
3ወንድሞች መጥተው በእውነት እንደምትሄድ ሲመሰክሩልኝ እጅግ ሀሴት አደረግሁኝ።
4ልጆቼ በእውነት መንገድ እየሄዱ እንደሆነ ከመስማት የበለጠ ደስታ የለኝም።
5የተወደድክ ሆይ ለወንድሞችም ሆነ ለእንግዶች በምታድርገው ነገር ስላለህ ታማኝነት
6ሁሉም በጉባኤ ፊት ይመሰክሩልሀል።ለእግዚአብሔር እንደሚገባ በጉዞአቸው በመደገፍህ መልካም አድርገሀል።
7ምክንያቱም ለተጠሩለት ስም አገልግሎት ሲወጡ ከአህዛብ ምንም አልወሰዱም።
8ስለዚህም የእውነት ማህበርተኞች እንሆን ዘንድ እንደነዚህ ያሉትን መርዳት ይገባናል።
9ስለአንድ ጉዳይ ለቤተክርስቲያን ጽፌ ነበር ነገር ግን በመካከላቸውአለቃ ሊሆን የሚወደው ዲዮትሪፈስ አይቀበለንም።
10ስለዚህ በምመጣበት ጊዜ ያደረገውን ነገርና እንዴት ባሉ ክፉ ቃላት በእኛ ላይ እንደተናገረ አልረሳም።ይህም አልበቃ ብሎት ወንድሞችን አይቀበልም ሊቀበሉ የሚፈልጉትንም ይከለክላቸዋል ከቤተክርስቲያንም ያስወጣቸዋል።
11የተወደድክ ሆይ መልካሙን እንጂ ክፉን አትምሰል። መልካም የሚያደርግ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው። ክፉን የሚያደርግ ሁሉ እግዚአብሔርን አላየውም።
12ለዲሜጥሮስ ሁሉም ይመሰክሩለታል እውነት እራሷም ትመሰክርለታልች። እኛም እንመሰክርለታለን የኛ ምስክርነት ደግሞ እውነት እንደሆነ ታውቃላችሁ።
13የምጽፍልህ ብዙ ነገር ነበረኝ ነገር ግን በወረቀትና በቀለም ልጽፍልህ አልፈለግሁም።
14ይልቁኑ ልጎበኝህ አስባለሁና በዚያን ጊዜ ፊት ለፊት እንነጋገራለን።
15ሠላም ለአንተ ይሁን። ወገኖችሰላምታ ያቀርቡልሀል። በአንተ ዘንድ ላሉት ወገኖች በስማቸው እየጠራህ ሠላምታ አቅርብልኝ።