መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

2ኛ ዮሐንስ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከሽማግሌው በእውነት ለምወዳችሁና እኔም ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ለሚወዱአችሁ ለተመረጥች እመቤትና ለልጆችዋ ።
2ይህም ፍቅር በውስጣችን ካለውና ለዘላለም ከእኛ ጋር ከሚሆነው እውነት የተነሳ ነው።
3በእውነትና በፍቅር ከእግዚአብሔር አብ ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ምህረትና ሠላም ከሁላችን ጋር ይሁን።
4ከልጆችሽ መካከል ከአብ በተቀበልነው ትዕዛዝ መሠረት በእውነት ሲሄዱ በማግኘቴ እጅግ ሀሴት አደርጋለሁ።
5እንግዲህ እመቤት አሁን አዲስ ትዕዛዝ እንደምሰጥ ሳይሆን እርስ በእርሳችን እንዋደድ ብዬ ከመጀመሪያው በነበረን ትዕዛዝ እለምንሻለሁ።
6ይህም በትዕዛዛቱ መሰረት ልንጓዝበት የሚገባን ፍቅር ነው። ይህ ትዕዛዝ ከመጀመሪያው እንደሰማችሁት ልትራመዱበት የሚገባ ትዕዛዝ ነው።
7ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማያምኑ ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ወጥተዋል። ይህም አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።
8ሙሉ ዋጋችሁን እንድትቀበሉ እንጂ እኛ ሁላችን የደክምንባቸውን ነገሮች እንዳታጡ ስለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
9በክርስቶስ ትምህርት ሳይጸና ዝም ብሎ ወደፊት የሚገሰግስ እግዚአብሄርን አያውቅም። በዚህ ትምህርት የሚጸና አብና ወልድ አሉት።
10ማንም ወደ እናንተ መጥቶ ይህን ትምህርት ባያስተምር ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አትፍቀዱለት ሠላምም አትበሉት።
11ምክንያቱም ሠላምታ የሚሰጠው ሁሉ በክፉ ሥራው ይካፈላል።
12የምጽፍላችሁ ብዙ ነገር ነበረኝ ነገር ግን በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልፈለግሁም። ነገር ግን ደስታችን ሙሉ ይሆን ዘንድ ወደ እናንተ ልመጣና ፊት ለፊት ላወራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
13የተመረጠችው እህትሽ ልጆች ሠላምታ ያቀርቡልሻል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።