1የእስራኤል ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፣
2ዳን፣ ዮሴፍ፣ ብንያም፣ ንፍታሌም፣ ጋድ፣ እሴር።
3የይሁዳ ወንዶች ልጆች፤ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፣ እነዚህን ጆስቱን ከከነዓን ሚስቱ ከሴዋ ወለደ። የበኩር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ሆነ፤ እግዚአብሔር ቀፈፈው።
4የልጁም ሚስት የነበረችው ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ ይሁዳም ባጠቃላይ አምስት ወንዶች ልጆች ነበሩት።
5የፋሬስ ወንዶች ልጆች፤ ኤስሮም፣ ሐሙል።
6የዛራ ወንዶች ልጆች፤ ዘምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ከልኮል፣ ዳራ፣ ባጠቃላይ አምስት ናቸው።
7የከሚር ወንድ ልጅ አካን፤ እርሱም ፈፅሞ መደምሰስ የነበረበት ነገር ሰርቆ በእስራኤል ላይ ጥፋት እንዲመጣ ያደረገ ነው።
8የኤታን ወንድ ልጅ፤ አዛርያ።
9የኤስሮን ወንዶች ልጆች፤ ይረሕምል፣አራም፣ካሌብ።
10አራም አሚናዳብን ወለደ፤አሚናዳብም የይሁዳ ሕዝብ መሪ የሆነውን ነአሶንን ወለደ፤
11ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ሰልሞን ቦዔንን ወለደ።
12ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ኢዮብይድ እሴይን ወለደ።
13የእሴይ ወንዶች ልጆች፤ የብኩር ልጁ ኤልያብ፣ ሁለተኛ ልጁ አሚናዳብ፣ ሦስተኛ ልጁ ሣማ፣
14አራተኛው ልጁ ናትናኤል፣ አምስተኛ ልጁ ራዳይ፣
15ስድስተኛ ልጁ አሳም፣ ሰባተኛ ልጁ ዳዊት።
16እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ። የጹሩያ ሦስት ወንዶች ልጆች አቢሳ፣ ኢዮአብና አሣኤል ነበሩ።
17አቢግያ አሜሳይን ወለደች፣ አባቱም ዬቴር የተባለ እስማኤላዊ ነበረ።
18የኤስሮም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባና እንዲሁም ከይሪዖት ወንዶች ልጆች ወለደ፥ ከዓዜባ የተወለዱት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። ያሳብ፣ ሶባብ፣ አርዶን፣
19ዓዙባ ስትሞት፣ ካሌብ ኤፍራታን አገባ፤ እርሷም ሆርን ወለደችለት።
20ሆርኡሪን ወለደ፤ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።
21ከዚህም በኋላ ኤስሮም ሥልሳ ዓመት ሲሆነው የገለዓድን አባት የማኪርን ልጅ አገባ፤ እርሷም ሠጉብን ወለደችለት።
22ሠጉብም ኢያዕርን ወለድደ፤ እርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት አተሞች ያስተዳድር ነበር።
23ይሁን እንጂ ጌሹና አራም፣ ቄናትንና በዙሪያዋ የሚገኑትን ሥልሳ መነደሮች ጨምሮ የኢያዕርን ከተሞች ነጠቁት። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባትየማኪር ዘሮች ነበሩ።
24ኤስሮም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ፣ ሚስቱ አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።
25የኤስሮም የበኩር ልጅ የይረሕምኤል ወንዶች ልጆች፤ የበኩር ልጁ ራም፣ ቡናህ፣ ኦሬን፣ ኦጼን፣ አኪያ።
26ይረሕምኤል ዓጣራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው፤ እርሷም የኦናምን እናት ነበረች።
27የይረሕምኤል የበኩር ልጁ የራም ወንዶች፤ መዓስ፣ ያሚን፣ ዔቄር።
28የኦናም ወንዶች ልጆች፤ ሸማይና ያዳ። የሸማይ ወንዶች ልጆች፤ ናዳብና አቢሱር።
29የአቢሱር ሚስት አቢካኢል ትባላለች፤ እርሷም አሕባንንና ሞሊድ የተባሉ ልጆች ወለደችለት።
30የናባድ ወንዶች ልጆች፤ ሴሌድ፣አፋይም፣ሴሌድ፣ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
31የአፋይም ወንድ ልጅ፤ይሸዒ።ይሽዒም ሶሳን ወለደ።ሶሳን አሕልይን ወለደ።
32የሸማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች፤ዬቴር፣ዮናታን፣ዬቴርም ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
33የዮናታን ወንዶች ልጆች፤ፌሌት፣ዛዛ። እነዚህ የይረሕምኤል ዘሮች ነበሩ።
34ሶሳን ሴቶች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም። እርሱም ኢዮሄል የተባለ ግብፃዊ አገልጋይ ነበርረው።
35ሶሳን ልጁን ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው፤ እርሷም ዓይታ የተባለ ወንድ ልጅ ወለደችለት።
36ዓታይ ናታንን ወለደ፣ናታንም ዛባድን ወለደ፣
37ዛባድ ኤፍላን ወለደ፤ ኤፍላል ዖቤድን ወለደ፤
38ዖቤድ ኢዩን ወለደ፤ ኢዩ ዓዛርያስን ወለደ፤
39ዓዛርያስ ኬሌስን ወለደ፤ ኬሌስ ኤልዓሣ ወለደ፤
40ኤልዓሣ ሲስማይን ወለደ፤ ሲስማይ ሰሎምን ወለደ፤
41ሰሎም የቃምያን ወለደ፤ የቃምያም ኤሊሳማን ወለደ።
42የይረሕምኤል ወንድም የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ የበኩር ልጁ ሞሳ ሲሆን፤ እርሱም ዚፍን ወለደ፤ ዚፍም መሪሳን ወለደ፤ መሪ ሳም ኬብሮንን ወለደ።
43የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ ቆሬ፣ ተፋዋ፣ ሬቄም፣ ሽማዕ።
44ሽማዕ ርችሐምን ወለደ፤ ረሐምም ዮርቅዓምን ወለደ። ሬቄም ሽማይን ወለደ፤
45ሽማይም ማዖንን ወለደ፤ ማዖንም ቤት ጹርን ወለደ።
46የካሌብ ቁባት ዔፋ ሐራንን፣ ሞዳን፣ ጋዜዝን ወለደች። ሐራንም ጋዜዝን ወለደ።
47የያህዳይ ወንዶች ልጆች፤ ሬጌም፣ ኢዮታም፣ ጌሻን፣ ፋሌጥ፣ ዔፋ፣ ሸዓፍ።
48የካሌብ ቁባት ማዕካ ሼቤርን፣ ቲርሐናን ወለደለችለት።
49እንዲሁም የመድማናን አባት ሸዓፍን፣ የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች። ካሌብ ዓክሳ የተባለች ልጅ ነበረችው።
50የኤፍራታ የበኩር ልጅ የሑር ወንዶች ልጆች ሦባል የቂርያት ይዓሪም አባት፤
51ሰልሞን የቤተልሔም አባት፤ ሐሬፍ የቤት ጋዴር አባት።
52የቂርያትይዓሪም አባት የሦባል ዘሮች፤ የመናሕታውያን ነዋሪዎች እኩሌታ፣ ሀሮኤ፤
53እንዲሁም የቂርያትይዓሪም ጎሣዎች፤ ይትራውያን፤ ፋታውያን፣ ሹማታውያን፣ ሚሽራውያን፤ ጾርዓውያንና ኤሽታኦውያን ከእነዚህ የመጡ ጎሣዎች ነበሩ።
54የሰልሞን ዘሮች፤ ቤተልሔም፣ ነጦፋውያን፣ ዓጣሮት ቤት ዮአብ፣ የመናሕታውያን እኩሌታ፣ ጾርዓውያን።
55በያቤጽ የሚኖሩ የጸሐፍት ጎሣዎች ቲርዓውያን፣ ሺምዓታውያን፣ ሡካታውያን። እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የመጡ ቄናውያን ናቸው።